Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ያዘጋጀው 16ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ።

ታህሳስ 16/04/2018 ዓ.ም, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ያዘጋጀው 16ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ። በውድድሩ ላይ በክፍለ ከተማው የሚገኙ አስሩም ወረዳዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ በባህላዊ ስፖርታዊ ጨዋታዎች የታጀበ ትርኢት ቀርቧል። ​የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ እንደተናገሩት ውድድሩ የተዘጋጀው የባህል ስፖርቶችን በመጠቀም በማህበረሰቡ መካከል ያለውን አንድነትና ወንድማማችነት እና የባህል ልውውጥ የበለጠ ለማጠናከር መሆኑን ገልፀዋል። አቶ አንተነህ አክለውም በውድድሩ በከተማ ደረጃ ለሚካሄደው የባህል ስፖርት ውድድር ክ/ከተማውን የሚወክሉ ስፖርተኞችን ይመረጣ በማለት ገልፀዋል። በጽ/ቤቱ የስፖርት ማህበራት ባለሙያ የሆኑት አቶ ፍሬው አሎ በበኩላቸው በውድድሩ ምርጥ እና ክፍለ ከተማውን ወክለው በከተማ አቀፍ የባህል ስፖርት ውድድር የሚሳተፉ ስፖርተኞችን ለመምረጥ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። ​በፌስቲቫሉ ላይ ስድስት የባህል ስፖርት አይነቶች ለውድድር ቀርበዋል። ​ገበጣ፡ (ባለ 12 እና ባለ 18 ቀዳዳ)፣ ቡብ፣​ ሻህ፣ ​ኩርቦና ቀስት ውርወራ የውድድሩ አካል ናቸው። ውድድሩ ወጣቶች የየአካባቢያቸውን የባህል እሴቶች የሚያንፀባርቁበትና እርስ በርስ የሚቀራረቡበት መድረክ ሆኖ ማለፉም ተገልጿል። በውድድሩ ብልጫ ያሳዩ ስፖርተኞች በቀጣይ ለሚካሄደው የከተማ አቀፍ ውድድር ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች