Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ የመደመር መንግስት የወጣቶች የፖናል ውይይት ተካሄደ

ጥቅምት 28, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በጠቅላይ ሚኒስቴር ዳ/ር አብይ አሕመድ በተፃፈው መደመር መንግስት መፅሐፍ ፅንሰ ሀሳብ ላይ ያተኮረ የወጣቶች የፖናል ውይይት አካሂዷል። በፖናል ውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ የመደመር መንግስት መፃሀፍ በሀገር በቀል እሳቤዎች የተዋቀረ ለሀገራዊ ችግሮች ሀገራዊ መፍትሔዎችን ያመላከተ መፅሐፍ ነው ብለዋል። መደመር፣ የመደመር መንገድ ፣ የመደመር ትውልድና የመደመር መንግስት መፅሀፎች ነገን የሚያሳዩና ብሩህ ተስፋን የሚፈነጥቁ ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎሉ መሆናቸውን አቶ ክብረአለም ገልፀዋል። በሌላ በኩል ለፖናል ውይይቱ መነሻ ሐሳብ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ሀላፊ አቶ ዳዊት ምንዳዬ በበኩላቸው የመደመር እሳቤ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እሳቤ መሆኑን ገልፀዋል። የመደመር መንግስት መፅሀፍ ተግባራትን በቅንጅት በማከናወን ለችግሮች ከራስ የመነጨ መፍትሔ በማስቀመጥ ለሀገር ብልፅግና ለመትጋት የሚያነሳሳ መሆኑን አቶ ዳዊት ተናግረዋል። የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ እንደተናገሩት የመደመር መንግስት መፅሀፍ ነገን የተሻለ ለማድረግ ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣና ለሀገር ብልፅግና እንዲተጋ መንገዶችን ያመላከተ መሆኑን ገልፀዋል። አቶ አንተነህ አክለውም አቅምን መጠቀም፣ ምዕናብን ከፍ ማድረግ፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ያስገኘው ውጤትና የፖለቲካ ባህልን ማሻሻል ይገባል ብለው ወጣቶች በሀገራቸው ሁለንተናዊ ብልፅግና አሻራቸውን ማስቀመጥ እንዳለባቸውም ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በመደመር መንግሰት የወጣቶች የፖናል ውይይት በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች