Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

ስፖርት የቱሪዝም ማዕከል እንዲሆን በትኩረት እየሰራን ነው-የልደታ ክ/ከተማ ስፖርት ምክር ቤት

ታህሳስ 12, 2018
ምክር ቤቱ የ2018 ዓ.ም 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል። የቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀመጡት የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚና የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት ስፖርት የቱሪዝም ማዕከል ሆኖ የሚጎበኝ እና ልምድ የሚወሰድበት እንዲሆን በትኩረት እየሰራን ነው ብለው ይህ ግብ እንዲሳካም ሁሉም በትኩረት ሊሰራ ይገባል በማለት ገልፀዋል። የስልጠና ማዕከላትን ማጠናከር ፣ ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ መገንባት እና ስፖርቱ ለስራ ዕድል ፈጠራ አጋዥ እንዲሆን ማስቻል በ2018 በጀት ዓመት በትኩረት እየተሰራበት መሆኑን የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በቀጣይም በላቀ እንደሚተገበር ተናግረዋል። ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት፣ የአካል ጉዳተኞችንና መስማት የተሳናቸውን ዜጎች፣ ወጣቶች፣ ታዳጊዎችና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የስፖርት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የበጀት ዓመቱ ትኩረት መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በማጠቃለያው ተናግረዋል። በማዘውተሪያ ስፍራዎች የማህበረሰቡን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል። የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት እንሰራለን በማለት ተናግረዋል። በዕለቱም በዘርፉ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት የዋንጫ ሽልማት ተሰጥቷል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች