Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

ባለፍት 6 ወራት በስነ-መግባር የታነፀ ብቁ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት መሰራቱን የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ገለፀ።

ጥር 4/4/2018 ዓ.ም, 2018
ባለፍት 6 ወራት በስነ-መግባር የታነፀ ብቁ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት መሰራቱን የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ገለፀ። ጽ/ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወር አፈፃፀሙን ገምግሟል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ በግምገማው ወቅት እንደተናገሩት ባለፍት 6 ወራት ማህበራዊ መስተጋብርን በማጠናከር አንድነት ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የበለጠ ለማጠናከር በልዩ ትኩረት ተሰርቷል ብለዋል። አቶ አንተነህ አክለውም በስነ-መግባር የታነፀ የሰላም እሴቶቻችን የሚተገብሩ ጤናማ ብቁ ተወዳዳሪና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በትኩረት መሰራቱን ገልፀዋል። ስፖርቱ ማህበራዊ መሰረት እንዲኖረው በማድረግ ረገድ ሰፊ ስራ ተሰርቷል ያሉት አቶ አንተነህ በቀጣይም ለዘርፍ እድገት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ስራዎች በማከናወን ዜጎችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ እንሰራለን በማለት ገልፀዋል። አቶ አንተነህ አክለውም ወጣቱ በስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆን የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ምዝገባና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል። ወጣቱን በጎ ፈቃድ ስራዎችን ተሳታፊ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የማድረግ ተግባር መከናወኑን አቶ አንተነህ ገልፀዋል። የስፖርት መሰረተ ልማቶችንም ለማስፋት ከምንጊዜውም በላይ መሰራቱን ኃላፊው ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት በ6 ወራት ስፖርት የሁሉም ዜጋ የእለት ከእለት ተግባር እንዲሆን ለማስቻል በዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን መፈጠሩን ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች