Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ የሳዳት ጀማል መታሰቢያ የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ

ታህሳስ 5, 2018
የሳዳት ጀማል መታሰቢያ የጤና ቡድን የእግር ኳስ ውድድሩን የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ጋር በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በውድድሩ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ታዋቂ 8 የጤና የእግር ኳስ ቡድኖች ይሳተፉበታል። በውድድሩ ማስጀመሪያ የቀድሞው የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ፍቅሩ ተፈራ፣ ጌታቸው ካሳ (ቡቡ)፣ ፋሲል አብርሃ ፣ በኢትዮጲያ የመጀመሪያው የቅርፅ ውድድር ሻምፒዮን ሀብትሽ ፊትነስ እና ሌሎችም ስመ- ጥር ስፖርተኞች ተገኝተዋል። የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ተገኝተው ባስተላለፍት መልዕክት እንደተናገሩት ሳዳት ጀማል በኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን በግብ ጠባቂነትና በአሰልጣኝነት በመሳተፍ ለኢትዮጲያ እግር ኳስ አሻራውን ያሳረፈ ተጨዋች ነበረ ብለው ውድድሩም ይህንን የሀገር ባለውለታ ለመዘከር መዘጋጀቱን ገልፀዋል። አቶ አንተነህ አክለውም በውድድሩ ሳዳት ጀማልን ከማስታወስ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የጤና ቡድኖች መካከል አንድነትን፣ ወንድማማችነትንና አብሮነትን ለማጠናከርም ታስቦ መዘጋጀቱን ገልፀው ውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነትን ተላብሶ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የየድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል። የስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ስክንድር ጋሻው በበኩላቸው ትልቅ ዓላማ ያለው የሳዳት ጀማል መታሰቢያ ውድድር ስፖርታዊ ጨዋነትን ተላብሶ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የስፖርት ቤተሰብ አስተዋፆ እንዲያደርግ አሳስበዋል። የስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ማስተር በፍቃዱ ታደሰ(ኢሱዬ) በበኩላቸው የሳዳት ጀማል መታሰቢያ የእግር ኳስ ውድድር ለ1 ወር የሚቆይ መሆኑን ገልፀው ውድድሩም በስኬት እንዲጠናቀቅም ሁሉም የየድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች