Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ የታዳጊ ወጣቶች የጤና ምርመራ መካሄድ ጀመረ

ታህሳስ 8, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት  የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ፕሮጀክት ልማት ስልጠና ጣቢያ ሰልጣኞች የጤና እና የእድሜ ምርመራ  አካሄደ ጽ/ቤቱ በቢሪሞ ሜዳ ያስጀመረው ምርመራ የጥርስ ጤንነት እና የአካላዊ ቁመና ጤነኝነት በመለካት የሰውነት መጠነ ዙሪያ ምርመራ መሆኑ ተመልክቷል ተተኪ ሰፓርተኞች በብዛትና በጥራት ለማፍራት ከሚደረጉ ዙርፈ ብዙ እንቅስቃሴ አንዱ  የታዳጊ ወጣቶች የጤና ምርመራ መሆኑን የስፓርት ትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ ወ/ሪት እየሩሳሌም ያቆብ ገልጸዋል ምርመራው ለታዳጊ ወጣቶች የአመጋገብ ሁኔታ እና አካላዊ ጤንነታቸውን ለማየት የሚያስችል መሆኑን የገለጹት የከተማ ቢሮ የሕክምና ቡድን መሪ ወይዘሮ ሐያት ኪያር  የተተኪ ስፓርተኞችን ዕድሜ ምርመራ በሁሉም ክፍለ ከተሞች መካሄድ እንዳለበት ገልጸው የልደታን ስራ አድንቀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች