Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ "ስልጡን ወጣት ለከተማ እድገትና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፤

ጥር 02/05/2018 ዓ.ም, 2018
በልደታ ክ/ከተማ "ስልጡን ወጣት ለከተማ እድገትና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፤ የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት እና የልደታ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ከወጣቶች ጋር ውይይት አካሂዷል። የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አሰፋ ቶላ እንደገለፁት የሁሉም ነገር መሰረት የሆነውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ወጣቶች የሚሪነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለው በዚህም ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ወጣቶች የሰላም እሴቶችን በመጠበቅ እና በማስጠበቅ የሀገር ሰላምና ብልፅግና እንዲረጋገጥ የየድርሻቸሁን መወጣት አለባቹህ ብለዋል አቶ አሰፋ። ሰላም የልማቶቻችን ሁሉ መሰረት በመሆኑ እንደ አይናችን ብሌን ልንጠብቀው ይገባል ያሉት አቶ አሰፋ ወጣቶች ከፀጥታ አካሉ ጋር በመቀናጀት ሰላሙን ሊጠብቅ እንደሚገባ ተናግረዋል። የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ እንደተናገሩት ስልጡን ወጣት ግጭትን ለመከላከልና ለመፍታት እንዲሁም የረዥም ጊዜ ሰላምና እድገትን ለማስፈን ጠቃሚ ሀይል ነው ብለው ወጣቱ ማህበራዊ ውህደትን በመጠበቅ ኢኮኖሚያዊ አቅምን መገንባት አለበት በማለት ተናግረዋል። አቶ አንተነህ አክለውም ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላም ግንባታና ሁለንተናዊ ብልፅግና መሰረት ነው ያሉ ሲሆን ወጣቱ አሰባሳቢ እና ገዥ ትርክትን በማቀንቀን ለሀገር ግንባታ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። በሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የሰላም እሴት ግንባታ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ በበኩላቸው ሰላም የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ በጋራ ልንጠብቀው ይገባል ብለዋል። ወጣቶች በበኩላቸው ለሀገር ግንባታና ብልፅግና በትጋት እንሰራለን በማለት ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች