Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

«ተስፋን እንትከል» በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን የችግኝ መትከያ የጉድጓድ ቁፋሮ ንቅናቄ አካሂደዋል።

ሰኔ 20/10/18, 2018
«ተስፋን እንትከል» በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን የችግኝ መትከያ የጉድጓድ ቁፋሮ ንቅናቄ አካሂደዋል። ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ቅድመ ዝግጅት ይሆን ዘንድ በተዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር ላይ በርካታ የክፍለ ከተማው ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል። የነገዋን ኢትዮጵያ በአረንጓዴ መልክ የመቅረጽ አላማ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፓለቲካ ና አቅም ግንባታ ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ እንደገለጹት፣ ይህ መርሃ ግብር የአካባቢ ጥበቃን ከማጠናከር ባለፈ በወጣቶች ዘንድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህልን ለማሳደግ ያለመ ነው። ወጣቱ ዛሬ የሚቆፍረው ጉድጓድና ነገ የሚተክለው ችግኝ የሀገርን ተስፋ የማለምለም ሂደት አካል ነው፤ ለዚህም ነው መሪ ቃላችንን 'ተስፋን እንትከል' ያደረግነው» ሲሉ ገልጸዋል። የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግዛው አለሙ እንደገለጸው ዛሬ የቆፈርነው እያንዳንዱ ጉድጓድ ነገ ለምናስቀምጠው አረንጓዴ አሻራ እና ለምንተክለው የሀገር ተስፋ መሰረት ነው። ወጣትነት ጉልበት ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚተርፍ አቅም መሆኑን በተግባር አሳይታችኋል ብለዋል። የክ.ከተማው የወጣት ክንፍ ሀላፊ ወጣት ሳሙኤል ዋለልኝ የወጣቱ ጉልበትና ጊዜ ለበጎ ፍቃድ አገልግሎት መዋሉ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። ዋናው ትኩረት ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን፣ የተተከሉትን ችግኞች ተንከባክቦ ማሳደግና ውጤት ማየት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው አገራዊ ጥሪ ላይ የበኩላቸውን አሻራ በማሳረፋቸው ደስታ እንደተሰማቸው፣ የተቆፈሩት ጉድጓዶች ለሚተከሉ የችግኝ ዓይነቶች ተስማሚ ሆነው መዘጋጀታቸውን፣ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ማሳደግ ላይም በኃላፊነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች