Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤትና በአቢሲኒያ ባንክ አዘጋጅነት የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ

ታህሳስ 19/04/18, 2018
በልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤትና በአቢሲኒያ ባንክ አዘጋጅነት የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ በክ/ከተማው አስተባባሪነት ታላቁ የአቢሲኒያ ዋንጫ እንደ ሀገር በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ዲስትሪክቶች ያሳተፈ የእግር ኳስ ውድድር ተጀምሯል። በውድድሩ ማስጀመሪያ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ እንደተናገሩት የክ/ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት እና አቢሲኒያ ባንክ በስፖርቱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታውሰው ዛሬ የተጀመረው የእግር ኳስ ውድድርም የዚሁ አካል መሆኑን ገልፀዋል። አቶ አንተነህ አክለውም ስፖርት አንድነትን፣ ወንድማማችነትንና አብሮነትን የሚያጠናክር ነው ብለው በውድድሩ የሚሳተፉ ስፖርተኞችም ስፖርታዊ ጨዋነትን ተላብሰው ማጠናቀቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል። የአቢሲኒያ ባንክ የሰው ሀይል አስተዳደር ዋና ኦፊሰር አቶ ሰይፉ ቦጋለ እንደተናገሩት የውድድሩ ዓላማ በሰራተኞች መካከል አንድነትን አብሮነትንና የቡድን ስራን በላቀ በማጠናከር ምርታማነትን ለማሻሻል መሆኑን ገልፀዋል። አቶ ሰይፉ አክለውም ውድድሩ በ12 ቡድኖች መካከል በ4 ምድብ ተከፍሎ እንደሚካሄድ ገልፀው ውድድሩ ቤተሰባዊነትን በሚያንፀባርቅ መልኩ እንዲጠናቀቅም አሳስበዋል። የአቢሲኒያ ባንክ የሰራተኞች ማህበር ፕሬዜዳንት አቶ ሰለሞን በበኩላቸው ውድድሩ በሰራተኞች መካከል ትብብርና ወዳጅነት የሚገነባበት ነው ብለው ውድድሩም የሰላምን የአንድነትን እና የወንድማማችነት እሴትን የሚያጎለብት እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች