Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ከወጣቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።

ታህሳስ 9, 2018
የክፍለ ከተማው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ና በልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት በጋራ በተዘጋጀው መድረክ ከሁሉም ወረዳዎች ለተውጣጡ ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ መነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የምክክር መድረኩን የመሩት የክ/ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍታለው ከፍያለው ሲሆኑ ይህ የምክክር መድረክ የተዘጋደበት ዋነኛ አላማ ወጣቶችን የሰላም ግንባታ ዋነኛ አካል አድርጎ በማሳተፍ ረገድ ጉልህ እርምጃ መሆኑን በመድረኩ ተመላክቷል። ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ መጎልበት ዙሪያ ያላቸው ሚና የጉላ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ወጣቶች የሰላም ግንባታ ጥረቶችን በማጠናከር ረገድ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ ተገልጿል። የምክክር መድረኩ በሰላም እሴት ዙሪያ ያላቸውን አዎንታዊ ተፅዕኖ በማጎልበት የሰላም ባህልን ለማስፋፋት እንደሚያግዝ መሆኑ ተብራርቷል። የምክክሩ ተሳታፊ ወጣቶች እንደገለፁት በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ያላቸውን ሚና በጥልቀት እንዲገነዘቡና ለሰላም ሁለንተናዊ አቅማቸውን እንዲወጡ ዕድል እንደሚፈጥርላቸው ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች