Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የደም ልገሳ መርሐ-ግብር አካሄደ

ሰኔ 25/10/18, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የደም ልገሳ መርሐ-ግብር አካሄደ የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት አካል የሆነውን የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሂዷል። "በጎነት ለክቡር የሰው ልጅ ሕይወት" በሚል መሪ ቃል በተከናወነው በዚህ መርሐ-ግብር ላይ የጽሕፈት ቤቱ አመራሮች፣ ሠራተኞችና የክፍለ ከተማው ወጣቶች ተገኝተው ደማቸውን ለግሰዋል። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ግዛው አለሙ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቱ ማኅበረሰብ ለአገሩና ለወገኑ ያለውን አጋርነትና ፍቅር የሚያሳይበት ትልቅ መድረክ ነው። ደም መለገስ ደግሞ ከአንድ በጎ ተግባር በላይ የአንድን ወገን ሕይወት ከሞት የመታደግ ታላቅ ሰብአዊ ኃላፊነት በመሆኑ፣ የክፍለ ከተማው ወጣቶች ለቀረበላቸው ጥሪ በሰጡት ፈጣን ምላሽ ደስታቸውን ገልጸዋል። በዕለቱ በፈቃደኝነት ደማቸውን የለገሱ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት፣ በክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ-ግብር ላይ በመሳተፍ ደም በመለገሳቸው ትልቅ የሕሊና እርካታ እንዳገኙ ጠቁመው፤ መሰል የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል። ጽሕፈት ቤቱ በክረምት ወቅት ካቀዳቸው ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች መካከል ይህ የደም ልገሳ መርሐ-ግብር አንዱና ዋነኛው ሲሆን፣ በቀጣይም ወጣቱን ያሳተፉ ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ አቀፍ ልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ታውቋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች