Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ የሳዳት ጀማል መታሰቢያ የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ

የሳዳት ጀማል መታሰቢያ የጤና ቡድን የእግር ኳስ ውድድሩን የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ጋር በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በውድድሩ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ታዋቂ 8 የጤና የእግር ኳስ ቡድኖች ይሳተፉበታል። በውድድሩ ማስጀመሪያ የቀድሞው የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ፍቅሩ ተፈራ፣ ጌታቸው ካሳ (ቡቡ)፣ ፋሲል አብርሃ ፣ በኢትዮጲያ የመጀመሪያው የቅርፅ ውድድር ሻምፒዮን ሀብትሽ ፊትነስ እና ሌሎችም ስመ- ጥር ስፖርተኞች ተገኝተዋል። የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ተገኝተው ባስተላለፍት መልዕክት እንደተናገሩት ሳዳት ጀማል በኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን በግብ ጠባቂነትና በአሰልጣኝነት በመሳተፍ ለኢትዮጲያ እግር ኳስ አሻራውን ያሳረፈ ተጨዋች ነበረ ብለው ውድድሩም ይህንን የሀገር ባለውለታ ለመዘከር መዘጋጀቱን ገልፀዋል። አቶ አንተነህ አክለውም በውድድሩ ሳዳት ጀማልን ከማስታወስ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የጤና ቡድኖች መካከል አንድነትን፣ ወንድማማችነትንና አብሮነትን ለማጠናከርም ታስቦ መዘጋጀቱን ገልፀው ውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነትን ተላብሶ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የየድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል። የስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ስክንድር ጋሻው በበኩላቸው ትልቅ ዓላማ ያለው የሳዳት ጀማል መታሰቢያ ውድድር ስፖርታዊ ጨዋነትን ተላብሶ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የስፖርት ቤተሰብ አስተዋፆ እንዲያደርግ አሳስበዋል። የስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ማስተር በፍቃዱ ታደሰ(ኢሱዬ) በበኩላቸው የሳዳት ጀማል መታሰቢያ የእግር ኳስ ውድድር ለ1 ወር የሚቆይ መሆኑን ገልፀው ውድድሩም በስኬት እንዲጠናቀቅም ሁሉም የየድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ"ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የማስ ስፖርት ተካሄደ

ፕሮግራሙን የክ/ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል። የክ/ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ እና የዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ጢቂ ድሪባ በፕሮግራሙ ባደረጉት ንግግር ገዥ ትርክትና የሀሳብል ልዕልናን እውን በማድረግ የሀገር ከፍታን ማረጋገጥ አለብን ብለው አንድነትን ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን በማጠናከር የሀገራችንን ብልፅግና ማረጋገጥ ከሁላችንም ይጠበቃል በማለት ገልፀዋል። ገዥ ትርክትን በመገንባት የሀገር ግንባታ ጉዞን ማሳለጥ አለብን ያሉት አቶ ጢቂ በጋራ ትርክቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የብዝሀ ባህል፣ ቅርስና ታሪክ ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጲያን ብልፅግና እውን ማድረግ አለብን ሲሉ ገልፀዋል። የወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ እንደተናተገሩት የማስ ስፖርት ጤናን ከመጠበቅ ባለፈ አንድነትን ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና አለው ብለው በዘርፉ ጤናው የተጠበቀ እና ጤናማ አስተሳሰብን የተላበሰ ትውልድ ለመገንባት በትኩረት እየሰራን ነው ሲሉ ገልፀዋል። ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ ወሳኝ ስለሆነ መሰል ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እናጠናክራለን ብለዋል አቶ አንተነህ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
"በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ" በልደታ ክ/ከተማ ዘመናዊ እና ዓለም አቀፍ ስንታንዳርድን የሚያሟላ የስፖርት ማዕከል ስራ ጀመረ

የስፖርት ማከሉ ከሌሎች የስፖርት ማዕከላት ለየት የሚያደርገው ራሱን የቻለ አይስ ባዝ ያለው በመሆኑ ነው። የስፖርት ማዕከሉ ብቁ ፣ ጤናማ ፣ተወዳዳሪ እና አምራች የሆነ አገልጋይ ለመፍጠር ታልሞ የተገነባ ነው።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በ15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድርና ፌስቲቫል ተሳታፊ የነበረው የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች 2ኛ ደረጃ በመያዝ ተሸላሚ ሆነ።

እንኳን ደስ አላቹህ!! 27 ወርቅ፣ 18 ብር እና 12 የነሀስ መዳሊያዎች በመሰብሰብ የልደታ ክ/ከተማ 2ኛ ሆኖ ወድድሩን አጠናቋል። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በሽብርቅ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች 1ኛ ሆኖ አጠናቋል። በተገኘው ውጤት የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም ይህ ውጤት እንዲመጣ ስትሰሩ ለነበራቹህ እና ለክፍለ ከተማው ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላቹህ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም "በአዲስ ዕይታ የልደታን ከፍታ ማረጋገጥ" የሚል መርህን ይዘን በሁሉም ዘርፍ ውጤት ለማምጣት እየሰራን ነው ብለዋል። ክ/ከተማው 16ኛውን መስማት የተሳናቸውና የአካል ጉዳተኞች ለማዘጋጀት ከየካ ክፍለ ከተማ ጋር የአርማ ርክክብ አድርጓል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ የመደመር መንግስት የወጣቶች የፖናል ውይይት ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በጠቅላይ ሚኒስቴር ዳ/ር አብይ አሕመድ በተፃፈው መደመር መንግስት መፅሐፍ ፅንሰ ሀሳብ ላይ ያተኮረ የወጣቶች የፖናል ውይይት አካሂዷል። በፖናል ውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ የመደመር መንግስት መፃሀፍ በሀገር በቀል እሳቤዎች የተዋቀረ ለሀገራዊ ችግሮች ሀገራዊ መፍትሔዎችን ያመላከተ መፅሐፍ ነው ብለዋል። መደመር፣ የመደመር መንገድ ፣ የመደመር ትውልድና የመደመር መንግስት መፅሀፎች ነገን የሚያሳዩና ብሩህ ተስፋን የሚፈነጥቁ ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎሉ መሆናቸውን አቶ ክብረአለም ገልፀዋል። በሌላ በኩል ለፖናል ውይይቱ መነሻ ሐሳብ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ሀላፊ አቶ ዳዊት ምንዳዬ በበኩላቸው የመደመር እሳቤ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እሳቤ መሆኑን ገልፀዋል። የመደመር መንግስት መፅሀፍ ተግባራትን በቅንጅት በማከናወን ለችግሮች ከራስ የመነጨ መፍትሔ በማስቀመጥ ለሀገር ብልፅግና ለመትጋት የሚያነሳሳ መሆኑን አቶ ዳዊት ተናግረዋል። የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ እንደተናገሩት የመደመር መንግስት መፅሀፍ ነገን የተሻለ ለማድረግ ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣና ለሀገር ብልፅግና እንዲተጋ መንገዶችን ያመላከተ መሆኑን ገልፀዋል። አቶ አንተነህ አክለውም አቅምን መጠቀም፣ ምዕናብን ከፍ ማድረግ፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ያስገኘው ውጤትና የፖለቲካ ባህልን ማሻሻል ይገባል ብለው ወጣቶች በሀገራቸው ሁለንተናዊ ብልፅግና አሻራቸውን ማስቀመጥ እንዳለባቸውም ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በመደመር መንግሰት የወጣቶች የፖናል ውይይት በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ''በጎነት እና አብሮነት ለኢትዮጲያ ከፍታ'' በሚል መሪ ቃልየደም ልገሳ መርሃ-ግብር አካሄደ።

የልደታ ክፍለ ከተማ የወጣቶች ክንፍ የክፍለ ከተማ ወጣቶችን በማስተባበር በሜክሲኮ አደባባይ 150 በላይ ወጣቶች የደም ልገሳ አካሂደዋል ። የልደታ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ሳሙኤል ዋለልኝ እንደገለፀው የሰው ህይወት ለማዳን የወጣቶች ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዉ የልደታ ብልፅግ ፓርቲ ወጣቶች በክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብሩ ከፍተኛ የሆነ ተግባራትን እያከናወኑ ሲሆን የዛሬዉ የደም ልገሳ በሁሉም ወረዳዎች ሲካሄድ የነበረ እና የሚቀጥል ሲሆን ወጣቶች ከደም ልገሳ ከማድረግ ባለፈ የአካባቢያቸውን ሰላም ከማረጋገጥና ስራ ፈጥረው በመስራት እና የስራ ባህልን በማዳበር ሰርቶ መለወጥን ባህሉ ያደረገ ወጣት መፍጠርና በማንኛውም አግባብ ለበጎ ተግባር ፊት የሚቆም ወጣቶች ማፍራት ላይ በርካታ ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

image
image
image
image