Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ “ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ

ሀምሌ 11/11/2018, 2018
በልደታ ክፍለ ከተማ “ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ የልደታ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ከወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር፣ “ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ከሁሉም ወረዳ ወጣቶች ጋር የጋራ የውይይት መድረክ አካሄደ። የውይይት መድረኩ ዋና ዓላማ ወጣቶች በአካባቢያቸው ሰላምና ደህንነት ግንባታ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግና ከጸጥታ አካላት ጋር ያላቸውን ቅንጅት ማጠናከር ነው። በመድረኩ ላይ ወጣቶች በአካባቢያቸው ሰላምና ጸጥታን የማስከበር ሥራ ላይ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው አጽንዖት ተሰጥቶታል። ከተማዋን አስተማማኝ ለማድረግም ወጣቱ ከአስተዳደሩና ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት፣ ወቅቱን የዋጀ የጸጥታና የደህንነት ስምሪት መውሰድ እንደሚገባው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። ከዚህም በተጨማሪ በየአካባቢው በተፈጥሮና በሌሎች ምክንያቶች የሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ወጣቶች አስፈላጊውን ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው ተገልጿል። በተለይም ከደረቅ ወንጀሎች ጋር የተያያዙ ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል፣ ወጣቱ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ሰላማዊ የመኖሪያ ቀጠናዎችን (ብሎኮችን) ለመፍጠር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ቀርቧል። በመጨረሻም ተሳታፊ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላምና ጸጥታ በበላይነት ለመጠበቅና ለከተማዋ ሁለንተናዊ ብልፅግና በቁርጠኝነት ለመሥራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች