የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
በልደታ ክፍለ ከተማ በርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች የሚካሄዱባት የፌዴራሉ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫና በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት የሚ ገኙባት በመሆኑ የወጣቶችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማሳደግና ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ፣ ጤናማ ዜጋ ፣ ብቃት ያለው ስፖርተኛና ህብረተሰብን በመፍጠር የከተማዋን የሰላም ፣ የልማትና የዴሞክራሲ እድገት ማፋጠን ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡
ወጣቶች በሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ከማንኛውም ዜጋ በላይ ከፍተኛ ድርሻ ሊወጡ የሚችሉ ሀገር ገንቢና ተረካቢ፣ የነገ ተስፋዎችና በአገራችንም ሆነ በክፍለ ከተማችን በሚካሄዱ የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሪ ተዋናይ መሆናቸው እሙን ነው፡፡ በተመሳሳይም ስፖርት ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጾ ጉልህ ሲሆን በዘርፉ የስራ እድል ከማስገኘት ባሻገር ጤናማና አምራች ዜጋ በመፍጠር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
በልደታ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፖሊሲውን መሰረት ያደረገ የወጣቶች የልማትና የእድገት ፓኬጅ በመከለስና በመተግበር ወጣቶች በኢኮኖሚያዊ፤ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ ያላቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተቋምና ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት ወጣቶች የተዘዋዋሪ ፈንድ ብድር እና የመስሪያ ቦታ እንዲያገኙ እንዲሁም የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እንዲገነቡና ሁለገብ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ በርካታ ተግባራትን ማከናወን የተቻለ ሲሆን በዚህም ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
አቶ አንተነህ በፍቃዱ , የልደታ ክ/ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ